በማረሚያ ቤቶች የዜጎች ሰብአዊ አያያዝ መሻሻሉ ተገለፀ፡፡ የክልልማረሚያቤቶችኮሚሽነሮች፤አገራዊ ለውጡን ተከትሎ በማረሚያ ቤቶች የዜጎች ሰብዓዊ አያያዝ
መሻሻሉን ኢዜአ ያነጋገራቸው የተለያዩ ክልሎች ማረሚያ ቤት ኮሚሽነሮች ገልጸዋል። የሶማሌ ክልል ማረሚያ ቤቶች ኮሚሽን ኮሚሽነር በሽር አህመድ እንደሚሉት ከዓመታት በፊት በህግ
ጥላ ስር በሚገኙ ዜጎች ላይ የአካልና ሞራል ጉዳትን ጨምሮ በርካታ የመብት ጥሰቶች ይስተዋሉ ነበር።
ሰዎችን ያለ አግባብ ማሰርና ፍርድ መስጠት ፣ መደብደብ፣ ማሰቃየት እና አካል ማጉደል የማረሚያ ቤ
ቶች የዘወትር ስራ እንደነበርም አስታውሰዋለ።
በተደረገው ማሻሻያ ግን በማረሚያ ቤቶች ያሁሉ ግፍና በደል ማቆሚያ ተበጅቶለታል ብለዋል።
የኦሮሚያ ክልል ማረሚያ ቤቶች ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር ረታ በላቸው፤ ከአገራዊ ለውጡ በኋላ የ
ዜጎች ሰብዓዊ መብት አያያዝ ልዩ ትኩረት ተሰጥቶታል ብለዋል።
የተለያዩ አሰራሮችን በመዘርጋት የሰብዓዊ መብት አያያዙ የተሻለ እንዲሆን ለፖሊስ ሰራዊቱ ተከታታይ የ
ሙያ ስልጠና እየተሰጠ እንደሚገኝም ጠቁመዋል።
በክልሉ በሚገኙ ማረሚያ ቤቶች ያሉ ዜጎች አያያዝ ሰብዓዊ መብትን ያከበረ መሆኑን ከኢትዮጵያ ሰ
ብዓዊ መብት እና ከፌደራል ማረሚያ ቤቶች ኮሚሽኖች የተሰጡ ግብረ መልሶች ማሳያ ናቸው ያሉት
ደግሞ የአፋር ክልል ማረሚያ ቤቶች ኮሚሽን ኮሚሽነር ዑመር ኮቲና ናቸው።
የህግ ታራሚዎች ትምህርት እንዲማሩ፣ የሙያ ስልጠና እንዲያገኙ ከማረሚያ ቤት ሲወጡም ህግ አክባ
ሪ እንዲሆኑ እየተደረገ መሆኑ ተገልጿል።