ኢዜማ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዕጩ ተወዳዳሪ የነበሩ አባላቸዉ ህይወታቸዉ ማለፉን አስታወቀ፡፡
አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 25 ፣ 2013 ኢዜማ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዕጩ ተወዳዳሪ የነበሩ አባላቸዉ ህይወታቸዉ ማለፉን አስታወቀ፡፡
የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትህ (ኢዜማ) በሞረት እና ጅሩ ወረዳ እነዋሪ ምርጫ ወረዳ ፓርቲዉን በመወከል የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዕጩ ተወዳዳሪ የነበሩት ዶክተር ዘነበ ለማ (ባደረባቸው ህመም ምክንያት በተወለዱ በ60 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም በሞት መለየታቸዉን አስታዉቋል፡፡
የኢዜማ አባላት እና አመራር በ ዶክትር ዘነበ ለማሞት የተሰማዉን ጥልቅ ሐዘን መግለጹን የጠቀሰ ሲሆን ፤ ፓርተዉ ለወዳጅ ዘመዶቻቸው እና ለቅርብ ባልደረቦቻቸው ልባዊ መፅናናትን መመኘቱን በፌስቡክ ገጹ ገልጿል፡፡